የፍቅሬ ጅማሬ
ያስመራ ድምሬ
የፍቅራችን ፅዋይደገስ ምፅዋ
የፍቅሬ ጅማሬ
ያስመራ ድምሬ
የፍቅራችን ፅዋ
ይደገስ ምፅዋ
ለማ ይነገራል የናፍቆቴ ነገር
ከፊት እቃ አንግቼ ስጠብቅሽ ነበር
የላኩትን መልእክት ባያደርሱልሽ
ምንም ብንራራቅ ፍቅር አይጠፋሽ
ድንገት ቢለያየን ሞልቶብን ተከዜ
አይኖርም በፍቅር የባከነ ግዜ
አይኖርም በፍቅር የባከነ ግዜ
ይኸውልሽ ነያ የብርሀን ጮራ
ሰርጋችን አዲስ ላይ መልሳችን አስመራ
ሰርጋችን አዲስ ላይ መልሳችን አስመራ
ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ
ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ
አስጣልኩሽ ከስንቱ ተናንቄ
(ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ)
(ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ)
(አስጣልኩሽ ከስንቱ ተናንቄ)
ስንቱን አሳለፍነው በማናውቀው
ስንቱን አሳለፍነው በበረሀው
የገባው ሰው ሁሉ አዲመራ
(ስንቱን አሳለፍነው በማናውቀው
ስንቱን አሳለፍነው በበረሀው
የገባው ሰው ሁሉ አዲመራ)
አዲ...(አዲሳባ) መራ...(ከአስመራ)
አዲ...(አዲሳባ) መራ...(ከአስመራ)
መጣውልህ ብለው (አዲ-መራ) መተውብን ነበር (አዲ-መራ)
ድንበሩን ዘግተውት (አዲ-መራ) እንዳንነጋገር (አዲ-መራ)
ለከፋው ሰው ደራሽ (አዲ-መራ) ብርቱ ነው አካሚ (አዲ-መራ)
ላንቺም ለኔም መላሽ (አዲ-መራ) አድማጭና ሰሚ (አዲ-መራ)
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)
ሁለት አስርት አመት ቢመስልም ረጅም
የተዋደደ ሰው ፍቅር አያረጅም
ሜዳ ነው ዘንድሮ በልፍጠን ሹፌሩ
ሳምንትም አመት ነው ወደው ካፈቀሩ
ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ
ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ
አስጣልኩሽ ከስንቱ ተናንቄ
(ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ)
(ታግሼ በተስፋ ቀን ጠብቄ)
(አስጣልኩሽ ከስንቱ ተናንቄ)
ስንቱን አሳለፍነው በማናውቀው
ስንቱን አሳለፍነው በበረሀው
የገባው ሰው ሁሉ አዲመራ
(ስንቱን አሳለፍነው በማናውቀው)
(ስንቱን አሳለፍነው በበረሀው)
(የገባው ሰው ሁሉ አዲመራ)
አዲ...(አዲሳባ) መራ...(ከአስመራ)
አዲ...(አዲሳባ) መራ...(ከአስመራ)
መጣውልህ ብሎ (አዲ-መራ) መተውብን ነበር (አዲ-መራ)
ድንበሩን ዘግተውት (አዲ-መራ) እንዳንነጋገር (አዲ-መራ)
ለከፋው ሰው ደራሽ (አዲ-መራ) ብርቱ ነው አካሚ (አዲ-መራ)
ላንቺም ለኔም መላሽ (አዲ-መራ) አድማጭና ሰሚ (አዲ-መራ)
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)
መቼ ይደክመኛል (አዲ-መራ) ለመመላለሱ (አዲ-መራ)
ትኬቱን ልቁረጠው (አዲ-መራ) ሳይሞላ አውቶብሱ
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)
አዲ...(አዲመራ) መራ...(አዲመራ)