Mematsené

Teddy Afro

ቀና አታርጉኝ እኔን ከሔደች ትታው መማፀኔን
ተክዤ ልግፋው ይህ ሐዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔንእኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት
ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት
አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት

ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት
ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት
ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ
ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ

ገና በጊዜ በቀየው አድባር አብረን አድገን
ክፋት በሌለው በንፁ ፍቅር ተፈላልገን
ተዋደን ኖረን ባልነበረ አይነት በሚያስቀና
ልቧን ከልቤ ድንገት ለያየው ቀን መጣና

በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ
ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆነ እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታዲያ እንዴት ይሆን ወዳጅን ነግሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ያውም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታዲያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

ቀና አታርጉኝ እኔን ከሔደች ትታው መማፀኔን
ተክዤ ልግፋው ይህ ሐዘኔን
ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔን
እኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት
ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት
አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት

ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት
ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት
ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ
ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ

በዚህ አለም ሚዛን ነፍስ ያለ ፍቅር መች ይሞላል
በሌለሽበት ሲኖር ያላንቺ ቀን ይጎላል
እስኪ አውቀንበት ሰው ሳንፈልግ ሌላ ዳኛ
ብለን ለፍቅር ተይ እንገናኝ ዞረን እኛ

በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ
ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆነ እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታዲያ እንዴት ይሆን ወዳጅን ነግሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ

መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ
ያውም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ
ታዲያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ
ልብን መመለስ ወደ ድሮ