Yene Konjo (feat. Zeritu Kebede)

Eyob Mekonen , Zeritu Kebede

ከተመኘሁትም ካለምኩትም በላይ
ፍቅር አለ በህይወቴ
ሁሉም አንተን በማግኘቴከታገልኩለትም ከጣርኩትም በላይ
ደስተኛ ነኝ በህይወቴ
ሁሉም አንቺን በማግኘቴ

የኔ ቆንጆ ዉብ እኮ ነህ
የታላቅ ጥበብ ትዕይንት
የኔ ቆንጆ የምታምር
ልዩ ስራ ግሩም ፍጥረት
እወድሃለሁ መቼም ቢሆን
አንተ ለኔ ነህ ልዩ ሰው
እወድሃለሁ ዛሬም ነገም
አለውጥህም በምንም

የኔ ቆንጆ
የኔ ቆንጆ
የኔ ቆንጆ
የኔ ቆንጆ

ተስፋ ካደረኩት
ከልቤ እምነት በላይ
እውነት አየሁ በኛ ፍቅር
አንቺን ሰጠኝ እሱ ይክበር
ከሰማሁት ከጠበኩት በላይ
ሰላም አለ በኛ ፍቅር
አንተን ሰጠኝ እሱ ይክበር

የኔ ቆንጆ የነፍሴ አጋር
የእውነት ደስታን አፍላቂዬ
የኔ ቆንጆ ድንቅ ታእምር
አምላኬን ማመስገኛዬ
እወድሻለሁ መቼም ቢሆን
አንቺ ለኔ ነሽ ልዩ ሰው
እወድሻለሁ ዛሬም ነገም
አለዉጥሽም በምንም

የኔ ቆንጆ
የኔ ቆንጆ

የኔ ቆንጆ (የኔ ቆንጆ)
ድንቅ ታእምር (የኔ ቆንጆ)
አምላኬን ማመስገኛዬ
እወድሃለሁ መቼም ቢሆን
አንተ ለኔ ነህ ልዩ ሰው
እወድሃለሁ ዛሬም ነገም
አለዉጥህም በምንም