Berta

Yohana , Kassmasse

ቀና ልብ
እስኪቢዲብዳብዴ
ካሥማሠዮሐና

ጤና ይስጥልኝ ነግቷል
ፀሐይ ለሁሉ ወጥቷል
እይ ወደፊት
ወደፊት
ቀን ሌላ አዲስ መቷል
ማደጊያ ዕድል ሰቷል
ሂድ ወደፊት
ወደፊት
መልስ አይሆን ለድክመትህ
ምን ቢበዛ ምክንያትህ
ላያስቆም ከውድቀትህ
አስጥሎ
ካልነገርከው ጉልበትህ
አያደርስ ከመርካትህ
ቆሞ ፈቅ ማለትን
ከልክሎ
መች ጠፋና በእውነቱ
እንደ አቅምና እንደ እውቀቱ
ፈተናው በየቤቱ
ታድሎ
ዕድል ነው ከማለትህ
ከሰነፍ ማብራራትህ
ጎልቶ ይታያል ድክመትህ
አይሎ
ግን እውነትህ
ታስሮ ከእምነትህ
አትቆጥብ ከምኞትህ
ስኬት ነው እንደ ልኬትህ
ጣር ሞክር ይበራል
አዎ እድገትህ
ታስሮ ከእምነትህ

አትቆጥብ ከምኞትህ
ስኬት ነው እንደ ልኬትህ
ተጓዝ መች ይቀራል
አዎ የጣረም ይጠራል

በል በርታ
በርታ
በርታ
በል ወንድም በርታ በርታ
አይዞህ እንዳትረታ
በርታ
በርታ
በርታ
በል ወንድም በርታ በርታ
አይዞህ እንዳትረታ

በርቺ በሏት
ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ
ጥሯት
ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ
በርቺ በሏት
ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ
ጥሯት
ጥራት ነሽ ጥቁር ቀይ ዕንቁ (ካሥማሠ)
በርታ በይ ልንገርሽ ነገን ላንቺ (ላንቺ)
መልክ የንግሥቲቷም ውበት ያንቺ (ያንቺ)
እኛ ትናንት መስታወት ባየን ባንቺ (ባንቺ)
ሆነሽ አንቺም እንደሷ ባየን አንቺን (አንቺን)
ውብ ዓለም እንድትሆን የኛ ዓለም በርቺ (በርቺ)
አንድ መላ ነሽ የኛ አንቺ በርቺ (በርቺ)
ውብ ዓለም እንድትሆን የኛ አንቺ በርቺ (በርቺ)
አንድ መላ ነሽ የኛ ዓለም አንቺ (አንቺ)
ቀመር ለኛ ውሎ ደህና ብታበጅ
ላንቺ እንጂ ትላንትም ነገም ላንቺ
የኛ አለም አንደኛ ነች ሁሌም አዲስ
ካንቺ እንጂ ምንኖር ዘውትር መካስ
ቆንጅት እውነትሽ
ነው ከልብ እምነትሽ
ይታይ በዕውቀትሽ
እመቤትነትሽ
አይቆጠብ ምኞትሽ
ስኬት ነው እንደልኬትሽ
ለኔ ያልሽው ይበራል
እኅት ጥልቀትሽ
ሲዘል ከውበትሽ
ያነቃል ህይወትሽ
ክብርሽ ሴትነትሽ

አይቆጠብ ምኞትሽ
ስኬት ነው እንደልኬትሽ
መድረስ መች ይቀራል
አዎ የጣረም ይጠራል

በይ በርቺ
በርቺ
በርቺ
የኛ እኅት በርቺ በርቺ
አይዞሽ እንዳትረቺ
በርቺ
በርቺ
በርቺ
እኅቴም ጠንክሪ አንቺ
አይዞሽ እንዳትረቺ

በርቺ በሏት
ወንድም እሱም ይበርታ
ጥሯት
እኅት ዓለም ትበርታ
በርቺ በሏት
ወገን ሁሉም ይበርታ
ጥሯት
ነገም ይመርባታ
በርታ በይ ልንገርሽ ነገን ላንቺ (ላንቺ)
መልክ የንግሥቲቷም ውበት ያንቺ (ያንቺ)
እኛ ትናንት መስታወት ባየን ባንቺ (ባንቺ)
ሆነሽ አንቺም እንደሷ ባየን አንቺን (አንቺን)

በርታ አንተም በርታ
በርቺ አንቺም በርቺ
በርታ አንተም በርታ
በርቺ አንቺም በርቺ
በርታ አንተም በርታ
በርቺ አንቺም በርቺ
በርታ አንተም በርታ
በርቺ አንቺም በርቺ
በርታ አንተም በርታ
በርቺ አንቺም በርቺ

Daftar lirik lagu Yohana